የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ነህምያ 10

10
1ያተሙትም የሐካልያ ልጅ የሆነው አገረ ገዢው ነህምያ፥ ሴዴቅያስ።
2-8ከካህናት ወገን፦
ሠራያ፥ ዐዛርያ፥ ኤርምያስ፥
ፓሽሑር፥ አማርያ፥ ማልኪያ፥
ሐጡሽ፥ ሸባንያ፥ ማሉክ፥
ሐሪም፥ መሬሞት፥ አብድዩ፥
ዳንኤል፥ ጊነቶን፥ ባሩክ፥
መሹላም፥ አቢያ፥ ሚያሚን፥
መዓዝያ፥ ቢልጋይና ሸማዕያ።
9-13ከሌዋውያን ወገን፦
የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥
የሔናዳድ ጐሣ የሆነው ቢኑይ፥
ቃድሚኤል፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥
ቀሊጣ፥ ፐላያ፥ ሐናን፥
ሚካ፥ ረሖብ፥ ሐሻብያ፥
ዛኩር፥ ሼሬብያ፥ ሸባንያ፥
ሆዲያ፥ ባኒና በኒኑ።
14-27ከሕዝቡ መሪዎች ወገን፦
ፓርዖሽ፥ ፓሐትሞአብ፥
ዔላም፥ ዛቱ፥ ባኒ፥
ቡኒ፥ ዓዝጋድ፥ ቤባይ፥
አዶኒያ፥ ቢግዋይ፥ ዓዲን፥
አጤር፥ ሕዝቅያስ፥ ዓዙር፥
ሆዲያ፥ ሐሹም፥ ቤጻይ፥
ሐሪፍ፥ ዐናቶት፥ ኔባይ፥
ማግፒዓሽ፥ መሹላም፥ ሔዚር፥
መሼዛብኤል፥ ጻዶቅ፥ ያዱዐ፥
ፐላጥያ፥ ሐናን፥ ዓናያ፥
ሆሴዕ፥ ሐናንያ፥ ሐሹብ፥
ሀሎሔሽ፥ ፒልሐ፥ ሾቤቅ፥
ረሑም፥ ሐሻብና፥ ማዕሤያ፥
አኪያ፥ ሐናን፥ ዓናን፥
ማሉክ፥ ሐሪምና በዓና።
የተደረገው ስምምነት
28የቀሩትም ሰዎች፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች፥ የቤተ መቅደሱ መዘምራን፥ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና ለእግዚአብሔር ሕግ ታዛዦች የሆኑ በጐረቤት ከሚኖሩት የባዕዳን አገር ሕዝቦች ራሳቸውን የለዩ፥ ከሚስቶቻቸው፥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻቸው ጋር፥ 29እነዚህ ሁሉ ወንድሞቻቸው ከሆኑት መሪዎቻቸው ጋር ተባብረው በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ አማካይነት ለተሰጡት ለጌታችን ለእግዚአብሔር ትእዛዞች፥ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ሁሉ ታዛዦች እንደሚሆኑ በእርግማንና በመሐላ ቃል ገቡ።
30በአካባቢአችን ላሉት አሕዛብ ሴቶች ልጆቻችንን በጋብቻ እንደማንሰጥና ወይም የእነርሱን ሴቶች ልጆች ለወንዶች ልጆቻችን በጋብቻ እንደማንወስድ ቃል እንገባለን። #ዘፀ. 34፥16፤ ዘዳ. 7፥3።
31የባዕዳን አገር ሕዝቦች በሰንበት ቀን ወይም በሌሎች በዓላት እህልም ሆነ ሌላ የንግድ ሸቀጥ ይዘው ቢመጡ፥ ከእነርሱ አንገዛም። #ዘሌ. 25፥1-7፤ ዘዳ. 15፥1-2። በየሰባት ዓመት አንድ ጊዜ ምድሪቱን አናርስም፤ ያበደርነውንም ዕዳ ሁሉ እንሰርዛለን።
32በየዓመቱ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውል እያንዳንዳችን የጥሬ ብር አንድ ሦስተኛ እጅ በማምጣት እንሰጣለን። #ዘፀ. 30፥11-16።
33እንዲሁም ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ከዚህ የሚከተሉትን ነገሮች አሟልተን እናቀርባለን፦ ይኸውም የተቀደሰውን ኅብስት፥ በየዕለቱ መቅረብ የሚገባውን የእህል መባ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆኑትን እንስሶች፥ በሰንበት ቀኖች፥ አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ጊዜና በሌሎችም በዓላት የሚቀርበውን፥ ሌላውንም የተቀደሰ መባ ሁሉ፥ ለእስራኤል ሕዝብ ኃጢአት ማስተስረያ መቅረብ የሚገባውንና ለቤተ መቅደሱ የሚያስፈልገውን ሌላውንም ነገር ሁሉ አናስታጒልም።
34በሕጉ ስለ መሥዋዕት በተጻፈው መሠረት ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የሚቀርበው መሥዋዕት የሚቃጠልበትን የማገዶ እንጨት የትኞቹ ጐሣዎች ማቅረብ እንደሚገባቸው እኛ ሕዝቡ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ በየዓመቱ ዕጣ በማውጣት እንወስናለን።
35የእህላችንን መከር በምንሰበስብበት ወቅትና የዛፎቻችንን ፍሬ በምንለቅምበት ወራት በመጀመሪያ የደረሰውን እሸት፥ ወደ ቤተ መቅደስ እያመጣን እናበረክታለን። #ዘፀ. 23፥19፤ 34፥26፤ ዘዳ. 26፥2።
36ከእኛ እያንዳንዳችን የሚወለደውን የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን በማስረከብ፥ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን እናደርጋለን፤ እንዲሁም ከላሞቻችን፥ ከበጎቻችንና ከፍየሎቻችን የሚወለደውንም ጥጃና ግልገል ሁሉ የመጀመሪያውን ለእግዚአብሔር እንለያለን። #ዘፀ. 13፥2።
37ከሰበሰብነው መከር የመጀመሪያውን እህል ዱቄት ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን እንሰጣለን፤ ሌላውንም የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይትና የመሳሰለውንም ፍራ ፍሬ ሁሉ የመጀመሪያውን መባ አድርገን እናቀርባለን። #ዘኍ. 18፥21።
ከእርሻ መንደሮቻችን ግብር ለሚሰበስቡት ሌዋውያንም ምድራችን ከምታበቅለው የእህል መከር ዐሥራት እያወጣን እንሰጣለን። 38ዐሥራቱም በሚሰበሰብበት ጊዜ ትውልዳቸው ከአሮን ወገን የሆኑ ካህናት፥ ከሌዋውያኑ ጋር ይገኛሉ፤ ለቤተ መቅደሱም አገልግሎት ሌዋውያኑ ከሚሰበስቡት ዐሥራት ውስጥ እንደገና ከዐሥር አንዱን አወጣጥተው ወደ ቤተ መቅደሱ የዕቃ ግምጃ ቤት ያስገባሉ። #ዘኍ. 18፥26። 39የእስራኤል ሕዝብና ሌዋውያኑ የእህል፥ የወይን ጠጅና የወይራ ዘይት ስጦታዎችን ይዘው ንዋያተ ቅዱሳት ወደሚቀመጡበትና አገልጋዮቹ ካህናት፥ በር ጠባቂዎቹና መዘምራኑ ወደሚያርፉበት ዕቃ ግምጃ ቤት ማምጣት አለባቸው።
የእግዚአብሔርን ቤት ከቶ ቸል አንልም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ