ኢየሱስ የጢሮስን አካባቢ ትቶ ሄደ፤ በሲዶና በኩልም አድርጎ ዐሥር ከተሞች በሚባለው አገር ወደ ገሊላ ባሕር መጣ። በዚያ አንድ ደንቆሮና ድዳ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፤ እጁንም እንዲጭንበት ለመኑት። ኢየሱስም ሰውየውን ከሕዝቡ ለይቶ ለብቻው ወሰደና ጣቶቹን በሰውየው ጆሮዎች ውስጥ አገባ፤ ምራቁንም እንትፍ ብሎ የሰውዬውን ምላስ ዳሰሰ፤ ወደ ሰማይም አሻቅቦ አይቶ ቃተተና ሰውየውን “ኤፍታህ!” አለው፤ ፍቺውም “ተከፈት!” ማለት ነው። ወዲያውኑ ጆሮዎቹ ተከፈቱ፤ አንደበቱም ተፈታ፤ ያለአንዳች ችግርም አጥርቶ መናገር ጀመረ። ኢየሱስ ይህን ነገር ለማንም እንዳይናገሩ ሰዎቹን አዘዛቸው፤ ይሁን እንጂ፥ እንዳይናገሩ ባዘዛቸው መጠን በብዙ አብልጠው ያወሩ ነበር። የሰሙትም ሁሉ እጅግ በጣም በመደነቅ፦ “ሁሉን ነገር በመልካም አደረገ! ደንቆሮዎች እንዲሰሙ፥ ድዳዎች እንዲናገሩ ያደርጋል!” አሉ።
የማርቆስ ወንጌል 7 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የማርቆስ ወንጌል 7:31-37
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች