የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የማርቆስ ወንጌል 6:45-52

የማርቆስ ወንጌል 6:45-52 አማ05

ኢየሱስ ወዲያውኑ ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በጀልባ ሆነው ወደ ማዶ ወደ ቤተ ሳይዳ ተሻግረው እንዲቀድሙት አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ ከእነርሱ ተለይቶ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ። በመሸም ጊዜ ጀልባዋ በባሕሩ መካከል ነበረች፤ እርሱ ግን ብቻውን በምድር ላይ ነበረ። ደቀ መዛሙርቱ ከወደፊታቸው በሚነፍሰው ነፋስ ምክንያት መቅዘፍ ተቸግረው ሲጨነቁ አያቸው፤ ከሌሊቱም ከዘጠኝ እስከ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ባለው ጊዜ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ መጣ፤ አልፎአቸውም ሊሄድ ነበር። ነገር ግን እነርሱ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ሲሄድ አይተው መንፈስ መስሎአቸው ጮኹ። ሁሉም ባዩት ጊዜ ደነገጡ። እርሱ ግን ወዲያውኑ፦ “አይዞአችሁ! እኔ ነኝ! አትፍሩ!” አላቸው፤ ወደ ጀልባውም ገብቶ፥ ከእነርሱ ጋር በሆነ ጊዜ ነፋሱ ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ በጣም ተደነቁ። ታዲያ፥ ልባቸው ደንዝዞ፥ የእንጀራውን ተአምር ሳያስተውሉ ቀርተው ነው እንጂ ይህ ነገር ባላስገረማቸውም ነበር።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች