የማርቆስ ወንጌል 2:23-28

የማርቆስ ወንጌል 2:23-28 አማ05

በሰንበት ቀን ኢየሱስ በስንዴ እርሻ መካከል ያልፍ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ ሲሄዱ የስንዴ እሸት መቅጠፍ ጀመሩ። ፈሪሳውያንም “እነሆ፥ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ያልተፈቀደውን ስለምን ያደርጋሉ?” ሲሉ ጠየቁት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ዳዊት ከተከታዮቹ ጋር በተራበና በተቸገረ ጊዜ ምን እንዳደረገ አላነበባችሁምን? አብያታር የካህናት አለቃ በነበረበት ዘመን እርሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፥ ከካህናት በቀር ለሌሎች መብላት ያልተፈቀደውን፥ የተቀደሰውን የመባ ኅብስት በላ፤ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ሰዎች ሰጣቸው።” ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ሰንበት ለሰው ተሠራ እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም። እንዲሁም የሰው ልጅ ለሰንበትም ጌታዋ ነው።”

ተዛማጅ ቪዲዮዎች