የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የማርቆስ ወንጌል 15:33-37

የማርቆስ ወንጌል 15:33-37 አማ05

ከቀኑም ስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ። ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ኢየሱስ፦ “ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ትርጓሜውም “አምላኬ፥ አምላኬ! ለምን ተውከኝ?” ማለት ነው። በዚያም ቆመው ከነበሩት ሰዎች አንዳንዶቹ የእርሱን ጩኸት ሰምተው “እነሆ! ኤልያስን ይጠራል፤” አሉ። ከእነርሱም አንዱ ሮጠና ሆምጣጤ በሰፍነግ ሞላ፤ እንዲጠጣውም በመቃ ላይ አድርጎ ለኢየሱስ ሰጠውና “ቈይ እስቲ ኤልያስ መጥቶ ያወርደው እንደ ሆነ እንይ!” አለ። ከዚህም በኋላ ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ነፍሱም ከሥጋው ተለየች።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች