በአጠገቡ ያልፉ የነበሩትም ሰዎች ራሳቸውን በንቀት እየነቀነቁ እንዲህ እያሉ ይሰድቡት ነበር፦ “አዬ፥ አንተ ቤተ መቅደስን አፍርሰህ በሦስት ቀን የምትሠራው! እስቲ አሁን ከመስቀል ውረድና ራስህን አድን!” በዚህ ዐይነት የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራንም እርስ በርሳቸው እንዲህ እየተባባሉ ይዘባበቱበት ነበር፦ “ሌሎችን አድኖአል፤ ራሱን ግን ማዳን አይችልም! እርሱ መሲሑ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ እስቲ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እንይና እንመንበት!” እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎች ይሰድቡት ነበር።
የማርቆስ ወንጌል 15 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የማርቆስ ወንጌል 15:29-32
16 ቀናት
የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት እና ትንሣኤ በአራቱ ወንጌላት ውስጥ ተገልፆል። ይህ የፋሲካ በዓል የሚነግረን ፣ እንዴት ኢየሱስ ክርስቶስ መራራ ፅዋን፣ መከራን እና ስቃይን በመስቀል ላይ ተቀብሎ ከሞት በመነሳቱ በትንሳኤው ለአለም ሁሉ የምስራች ዜናን አበሰረ ። ይህ አጭር ቪዲዮ ፣ የእያንዳንዱ ቀን ታሪክ በምሳሌ ይገልፃል።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች