የማርቆስ ወንጌል 10:35-44

የማርቆስ ወንጌል 10:35-44 አማ05

የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “መምህር ሆይ፥ የምንለምንህን ሁሉ እንድታደርግልን እንፈልጋለን፤” አሉት። እርሱም “ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። እነርሱም “በመንግሥትህ ክብር አንዳችን በቀኝህ፥ አንዳችን በግራህ እንድንቀመጥ ፍቀድልን፤” አሉት። ኢየሱስ ግን “የምትለምኑትን አታውቁም፤ እኔ የምጠጣውን (የመከራ) ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን? እኔስ የምጠመቀውን ጥምቀት መጠመቅ ትችላላችሁን?” አላቸው። እነርሱም “አዎ፥ እንችላለን፤” አሉ። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእርግጥ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤ ነገር ግን በቀኜና በግራዬ መቀመጥን የምሰጥ እኔ አይደለሁም፤ ይህ የሚሰጠው እግዚአብሔር ላዘጋጀላቸው ሰዎች ብቻ ነው።” የቀሩት ዐሥሩ ይህን ሰምተው በያዕቆብና በዮሐንስ ላይ ተቈጡ። ኢየሱስ ሁሉንም ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “የአሕዛብ አለቆች የሕዝብ ገዢዎች ተብለው እንደሚጠሩና መሪዎቻቸውም በእነርሱ ላይ ሥልጣን እንዳላቸው ታውቃላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ ግን እንዲህ መሆን አይገባም፤ ከመካከላችሁ ትልቅ ሊሆን የሚፈልግ፥ አገልጋያችሁ መሆን አለበት፤ እንዲሁም ከመካከላችሁ የበላይ ሊሆን የሚፈልግ የሁሉም ባሪያ ይሁን።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች