የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ሚክያስ 5:10-15

ትንቢተ ሚክያስ 5:10-15 አማ05

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቀደም ብዬ ግን ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ ሠረገሎቻችሁንም እደመስሳለሁ። በምድራችሁ የሚገኙትን ከተሞች አጠፋለሁ፤ ምሽጎቻችሁንም ሁሉ አፈራርሳለሁ፤ መተታችሁን አጠፋለሁ፤ ሟርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ በመካከላችሁ አይገኙም። የተቀረጹ ጣዖቶቻችሁንና የምትሰግዱላቸው ዐምዶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ የእጆቻችሁ ሥራ ለሆኑ ጣዖቶች ከእንግዲህ ወዲህ አትሰግዱም። የአሼራን ምስል ከምድራችሁ እነቃቅላለሁ፤ ከተሞቻችሁንም አፈራርሳለሁ። ለእኔ አልታዘዝም ያሉትን መንግሥታት ሁሉ በታላቅ ቊጣዬ እበቀላቸዋለሁ።”