የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሚክያስ 5:10-15

ሚክያስ 5:10-15 NASV

“በዚያን ጊዜ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ ሠረገሎቻችሁን እደመስሳለሁ። የምድራችሁን ከተሞች እደመስሳለሁ፤ ምሽጎቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ። ጥንቈላችሁን አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አታሟርቱም። የተቀረጹ ምስሎቻችሁን፣ የማምለኪያ ዐምዶቻችሁንም ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ ለእጃችሁ ሥራ አትሰግዱም። የአሼራ ምስልን ዐምድ ከመካከላችሁ እነቅላለሁ፤ ከተሞቻችሁንም እደመስሳለሁ። ያልታዘዙኝን አሕዛብ፣ በቍጣና በመዓት እበቀላቸዋለሁ።”