የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የማቴዎስ ወንጌል 8:24-27

የማቴዎስ ወንጌል 8:24-27 አማ05

ታላቅ ዐውሎ ነፋስ በባሕሩ ላይ ስለ ተነሣ ማዕበሉ ጀልባይቱን ሊያሰጥማት ደረሰ፤ ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “ጌታ ሆይ! ልንጠፋ ነው፤ አድነን!” ብለው ቀሰቀሱት። እርሱም “እናንተ እምነት የጐደላችሁ! ስለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው። ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። ሰዎቹም ተደንቀው፥ “ነፋስና ባሕር እንኳ የሚታዘዙለት ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው?” አሉ።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች