“በጠባብዋ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚያስገባው በር ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነው። ወደዚያ የሚገቡትም ሰዎች ብዙዎች ናቸው። ወደ ሕይወት የሚያስገባው በር ግን ጠባብ ነው፤ መንገዱም አስቸጋሪ ነው፤ እርሱን የሚያገኙት ሰዎች ጥቂቶች ናቸው። “የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፥ በውስጣቸው ግን እንደ ነጣቂ ተኲላዎች ከሆኑት ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፤ እነርሱንም የምታውቁአቸው በሥራቸው ፍሬ ነው። ከእሾኽ ቊጥቋጦ የወይን ፍሬ፥ ከኮሸሽላስ የበለስ ፍሬ ይለቀማልን? እንዲሁም መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያፈራል፤ መጥፎ ዛፍ ግን መጥፎ ፍሬ ያፈራል። መልካም ዛፍ መጥፎ ፍሬ ማፍራት አይችልም፤ መጥፎ ዛፍም መልካም ፍሬ ማፍራት አይችልም። መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ፥ ተቈርጦ ወደ እሳት ይጣላል። ስለዚህ፥ ሐሰተኞች ነቢያትን በሥራቸው ፍሬ ታውቁአቸዋላችሁ። ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም፤ ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገባው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚፈጽም ነው። በፍርድ ቀን ብዙዎች፥ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን?’ ይሉኛል። እኔም በዚያ ቀን፥ ‘በጭራሽ አላውቃችሁም! እናንተ ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ወዲያ ራቁ!’ እላቸዋለሁ።
የማቴዎስ ወንጌል 7 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የማቴዎስ ወንጌል 7:13-23
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos