የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የማቴዎስ ወንጌል 7:1-6

የማቴዎስ ወንጌል 7:1-6 አማ05

ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በእናንተ ላይ እንዳይፈረድባችሁ፥ በማንም ላይ አትፍረዱ፤ በሌሎች ላይ በምትፈርዱበት ፍርድ፥ በእናንተም ላይ ይፈረድባችኋል፤ እንዲሁም በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል። በአንተ ዐይን ያለውን ግንድ ሳታይ፥ ስለምን በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጒድፍ ትመለከታለህ? ደግሞስ በአንተ ዐይን ግንድ እያለ፥ ወንድምህን ‘እስቲ በዐይንህ ያለውን ጒድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ? አንተ ግብዝ! አስቀድመህ በአንተ ዐይን ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በኋላ፥ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጒድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ። የተቀደሰውን ነገር ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቋችሁንም በዐሣማዎች ፊት አትጣሉ፤ ዐሣማዎቹ ዕንቋችሁን በእግራቸው ይረግጡታል፤ ውሾቹም ተመልሰው ይነክሱአችኋል።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች