ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በእናንተ ላይ እንዳይፈረድባችሁ፥ በማንም ላይ አትፍረዱ፤ በሌሎች ላይ በምትፈርዱበት ፍርድ፥ በእናንተም ላይ ይፈረድባችኋል፤ እንዲሁም በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል። በአንተ ዐይን ያለውን ግንድ ሳታይ፥ ስለምን በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጒድፍ ትመለከታለህ? ደግሞስ በአንተ ዐይን ግንድ እያለ፥ ወንድምህን ‘እስቲ በዐይንህ ያለውን ጒድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ? አንተ ግብዝ! አስቀድመህ በአንተ ዐይን ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በኋላ፥ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጒድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ። የተቀደሰውን ነገር ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቋችሁንም በዐሣማዎች ፊት አትጣሉ፤ ዐሣማዎቹ ዕንቋችሁን በእግራቸው ይረግጡታል፤ ውሾቹም ተመልሰው ይነክሱአችኋል። “ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ የሚለምን ሁሉ ይቀበላል፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ በር ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል። ከእናንተ መካከል ልጁ ዳቦ ቢለምነው፥ ድንጋይ የሚሰጠው ማነው? ዓሣ ቢለምነውስ፥ እባብ ይሰጠዋልን? እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፥ ለልጆቻችሁ መልካም ነገር መስጠትን ካወቃችሁ፤ ታዲያ፥ በሰማይ ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን አይሰጣቸውም! እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፥ እናንተም ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የሕግና የነቢያት ትምህርትም የሚሉት ይህንኑ ነው።
የማቴዎስ ወንጌል 7 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የማቴዎስ ወንጌል 7:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች