የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የማቴዎስ ወንጌል 28:1-8

የማቴዎስ ወንጌል 28:1-8 አማ05

ሰንበት ካለፈ በኋላ ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን (እሑድ) ጠዋት፥ በማለዳ መግደላዊት ማርያምና ሌላይቱ ማርያም መቃብሩን ለማየት ሄዱ። እነሆ፥ በድንገት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የጌታ መልአክ ከሰማይ ወርዶ መቃብሩ የተዘጋበትን ድንጋይ አንከባለለና በላዩ ተቀመጠ። የመልአኩ ፊት እንደ መብረቅ ያበራ ነበር፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። ጠባቂዎቹ መልአኩን ከመፍራት የተነሣ በመንቀጥቀጥ እንደ በድን ሆኑ፤ መልአኩ ግን ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፤ “እናንተስ አትፍሩ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትፈልጉ ዐውቃለሁ፤ እርሱ እዚህ የለም ቀደም ብሎ እንደ ተናገረው ተነሥቶአል። እዚህ የለም፤ ተቀብሮበት የነበረበትን ስፍራ ኑና እዩ። እንግዲህ በፍጥነት ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ‘ከሞት ተነሥቶአል! እነሆ፥ ወደ ገሊላ ቀድሞአችሁ ይሄዳል፤ በዚያ ታገኙታላችሁ!’ ብላችሁ ንገሩአቸው፤ እነሆ፥ ነግሬአችኋለሁ።” ከዚህ በኋላ ሴቶቹ በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ከመቃብሩ በፍጥነት ሄዱ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሊነግሩ ሮጡ።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች