የማቴዎስ ወንጌል 27:19-21

የማቴዎስ ወንጌል 27:19-21 አማ05

ከዚህም በላይ ጲላጦስ በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ ሌሊት በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ በንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት። በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች “በርባን ይለቀቅ! ኢየሱስ ይገደል!” ብለው እንዲጠይቁ ሕዝቡን አግባቡ። ገዢውም “ከሁለቱ የትኛውን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” ሲል ሕዝቡን እንደገና ጠየቀ። እነርሱም “በርባንን እንድትፈታልን እንፈልጋለን” ሲሉ መለሱ።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች