“በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ፥ እኔም በሰማይ ባለው አባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ። በሰው ፊት የሚክደኝን ሁሉ ግን እኔም በሰማይ አባቴ ፊት እክደዋለሁ። እኔ የመጣሁት፥ ሰላምን በምድር ላይ ለማምጣት አይምሰላችሁ፤ እኔ ጦርነትን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። እኔ የመጣሁት፥ ወንድ ልጅን በአባቱ ላይ፥ ሴት ልጅን በእናትዋ ላይ፥ ምራትን በዐማትዋ ላይ፥ በጠላትነት ለማስነሣት ነው። ስለዚህ የሰው ጠላቶቹ፥ የገዛ ቤተሰቦቹ ይሆናሉ። ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም። የገዛ ራሱን መስቀል ተሸክሞ የማይከተለኝ ሰው የእኔ ሊሆን አይገባውም። ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፤ ሕይወቱን ስለ እኔ የሚያጠፋት ሁሉ ግን ያድናታል። እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን አብን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ያገኛል። በእውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ ደቀ መዝሙር በመሆኑ፥ ከነዚህ ታናናሾች ለአንዱ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳ የሚሰጥ ሰው ዋጋውን አያጣም።”
የማቴዎስ ወንጌል 10 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የማቴዎስ ወንጌል 10:32-42
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos