የማቴዎስ ወንጌል 10:26-31

የማቴዎስ ወንጌል 10:26-31 አማ05

“እንግዲህ ሰዎችን አትፍሩ፤ የተሸፈነ መገለጡ አይቀርም፤ የተሰወረም መታወቁ አይቀርም። ስለዚህ እኔ በጨለማ የምነግራችሁን፥ እናንተ በብርሃን ተናገሩት፤ በሹክሹክታ የሰማችሁትንም በከፍተኛ ቦታ ላይ መጥታችሁ በይፋ አስተምሩ። ሥጋን ከመግደል አልፈው ነፍስን መግደል የማይችሉትን ሰዎች አትፍሩ፤ ይልቁንስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን አምላክ ፍሩ። ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ይሁን እንጂ፥ የሰማይ አባታችሁ ሳይፈቅድ፥ አንዲቱ ድንቢጥ እንኳ በምድር ላይ ወድቃ አትቀርም። የእናንተ ግን የራስ ጠጒራችሁ እንኳ የተቈጠረ ነው። እንግዲህ እናንተ ግን ከብዙ ድንቢጦች እጅግ ስለምትበልጡ ከቶ አትፍሩ።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች