የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የማቴዎስ ወንጌል 1:2-16

የማቴዎስ ወንጌል 1:2-16 አማ05

አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብ ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤ ይሁዳ ፋሬስንና ዛራን ትዕማር ከምትባል ሴት ወለደ፤ ፋሬስ ሔስሮንን ወለደ፤ ሔስሮንም አራምን ወለደ፤ አራም ዓሚናዳብን ወለደ፤ ዓሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ረዓብ ከምትባል ሴት ወለደ፤ ቦዔዝ ኢዮቤድን ሩት ከምትባል ሴት ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊት የኦርዮ ሚስት ከነበረችው ሰሎሞንን ወለደ፤ ሰሎሞን ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓም አቢያን ወለደ፤ አቢያ አሳፍን ወለደ፤ አሳፍ ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥ ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራም ዖዝያን ወለደ፤ ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታም አካዝን ወለደ፤ አካዝ ሕዝቅያስን ወለደ፤ ሕዝቅያስ ምናሴን ወለደ፤ ምናሴ አሞጽን ወለደ፤ አሞጽ ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስ የእስራኤል ሕዝብ ወደ ባቢሎን ተማርከው በሄዱበት ዘመን ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ። ከባቢሎን ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያል ዘሩባቤልን ወለደ፤ ዘሩባቤል አብዩድን ወለደ፤ አብዩድ ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄም አዞርን ወለደ፤ አዞር ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅ አኪምን ወለደ፤ አኪም ኤልዩድን ወለደ፤ ኤልዩድ አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛር ማታንን ወለደ፤ ማታን ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብ መሲሕ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያም እጮኛ የሆነውን ዮሴፍን ወለደ።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች