ትንቢተ ሚልክያስ 3:2-4

ትንቢተ ሚልክያስ 3:2-4 አማ05

ነገር ግን እርሱ እንደ ብረት ማቅለጫ እሳትና እንደ ልብስ ማጠቢያ ሳሙና ስለ ሆነ በእርሱ የመምጫ ቀን ጸንቶ መቆም የሚችልና እርሱስ ሲገለጥ በፊቱ መቆም የሚችል ማነው? እርሱ እንደ ብረት አቅላጭና እንደ ብር አንጥረኛ ፍርድን ለማጣራት ይቀመጣል፤ የሌዊንም ልጆች የጽድቅ መሥዋዕት ለማቅረብ እስከሚችሉ ድረስ እንደ ወርቅና እንደ ብር ያጠራቸዋል። የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ የሚያቀርቡት መሥዋዕት እንደ ቀድሞ ዘመንና እንዳለፉት ዓመቶች እግዚአብሔርን የሚያስደስት ይሆናል።