የሉቃስ ወንጌል 3:21-38

የሉቃስ ወንጌል 3:21-38 አማ05

ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስም ተጠመቀ፤ እርሱ ሲጸልይ ሳለ ሰማይ ተከፈተ፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ሆኖ በእርሱ ላይ ወረደ፤ በዚያኑ ጊዜ “አንተ የተወደድክ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ። ኢየሱስ የማስተማር ሥራውን ሲጀምር፥ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያኽል ሆኖት ነበር፤ ለሕዝቡ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ ይመስላቸው ነበር፤ ይኸውም ዮሴፍ የዔሊ ልጅ፥ ዔሊ የማቲ ልጅ፥ ማቲ የሌዊ ልጅ፥ ሌዊ የሚልኪ ልጅ፥ ሚልኪ የዮና ልጅ፥ ዮና የዮሴፍ ልጅ፥ ዮሴፍ የማታትዩ ልጅ፥ ማታትዩ የአሞጽ ልጅ፥ አሞጽ የናሆም ልጅ፥ ናሆም የኤስሊም ልጅ፥ ኤስሊም የናጌ ልጅ፥ ናጌ የማአት ልጅ፥ ማአት የማታትዩ ልጅ፥ ማታትዩ የሴሜይ ልጅ፥ ሴሜይ የዮሴፍ ልጅ፥ ዮሴፍ የዮዳ ልጅ፥ ዮዳ የዮናን ልጅ፥ ዮናን የሬስ ልጅ፥ ሬስ የዘሩባቤል ልጅ፥ ዘሩባቤል የሰላትያል ልጅ፥ ሰላትያል የኔሪ ልጅ፤ ኔሪ የሚልኪ ልጅ፥ ሚልኪ የሐዲ ልጅ፥ ሐዲ የቆሳም ልጅ፥ ቆሳም የኤልሞዳም ልጅ፥ ኤልሞዳም የዔር ልጅ፥ ዔር የዮሴዕ ልጅ፥ ዮሴዕ የኤሊዔዛር ልጅ፥ ኤሊዔዛር የዮራም ልጅ፥ ዮራም የማጣት ልጅ፥ ማጣት የሌዊ ልጅ፥ ሌዊ የስምዖን ልጅ፥ ስምዖን የይሁዳ ልጅ፥ ይሁዳ የዮሴፍ ልጅ፥ ዮሴፍ የዮናን ልጅ፥ ዮናን የኤልያቂም ልጅ፥ ኤልያቄም የሜልያ ልጅ፥ ሜልያ የማይናን ልጅ፥ ማይናን የማጣት ልጅ፥ ማጣት የናታን ልጅ፥ ናታን የዳዊት ልጅ፥ ዳዊት የእሴይ ልጅ፥ እሴይ የኢዮቤድ ልጅ፥ ኢዮቤድ የቦዔዝ ልጅ፥ ቦዔዝ የሰልሞን ልጅ፥ ሰልሞን የነአሶን ልጅ፥ ነአሶን የዓሚናዳብ ልጅ፥ ዓሚናዳብ የራም ልጅ፥ ራም የአርኒ ልጅ፥ አርኒ የሔጽሮን ልጅ፥ ሔጽሮን የፋሬስ ልጅ፥ ፋሬስ የይሁዳ ልጅ፥ ይሁዳ የያዕቆብ ልጅ፥ ያዕቆብ የይስሐቅ ልጅ፥ ይስሐቅ የአብርሃም ልጅ፥ አብርሃም የታራ ልጅ፥ ታራ የናኮር ልጅ፥ ናኮር የሰሩግ ልጅ፥ ሰሩግ የረዑ ልጅ፥ ረዑ የፌሌግ ልጅ፥ ፋሌቅ የዔቤር ልጅ፥ ዔቤር የሼላሕ ልጅ፥ ሼላሕ የቃይንም ልጅ፥ ቃይንም የአርፋክስድ ልጅ፥ አርፋክስድ የሴም ልጅ፥ ሴም የኖኅ ልጅ፥ ኖኅ የላሜሕ ልጅ፥ ላሜሕ የማቱሳላ ልጅ፥ ማቱሳላ የሔኖክ ልጅ፥ ሔኖክ የያሬድ ልጅ፥ ያሬድ የመላልኤል ልጅ፥ መላልኤል የቃይናን ልጅ፥ ቃይናን የሄኖስ ልጅ፥ ሄኖስ የሤት ልጅ፥ ሤት የአዳም ልጅ፥ አዳም የእግዚአብሔር ልጅ ነው ይሉ ነበር።