የሉቃስ ወንጌል 22:63-65

የሉቃስ ወንጌል 22:63-65 አማ05

በዚያን ጊዜ ኢየሱስን ይዘውት የነበሩ ሰዎች በእርሱ ላይ ያፌዙበትና ይደበድቡትም ነበር። ፊቱንም እየሸፈኑ፥ “ማን ነው የመታህ? ነቢይ ከሆንክ እስቲ ዕወቅ!” ይሉት ነበር። በእርሱም ላይ ብዙ ነገር እየተናገሩ ይሰድቡት ነበር።