የሉቃስ ወንጌል 22:24-26

የሉቃስ ወንጌል 22:24-26 አማ05

ቀጥሎም እነርሱ፥ “ከሁላችን የሚበልጥ ማን ነው?” እያሉ እርስ በርሳቸው ይከራከሩ ጀመር። ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “የዚህ ዓለም ነገሥታት በሕዝቡ ላይ ሥልጣን አላቸው፤ ገዢዎችም የሕዝቡ በጎ አድራጊዎች ይባላሉ፤ እናንተ ግን እንደ እነርሱ ልትሆኑ አይገባም፤ ይልቅስ ከእናንተ መካከል ትልቅ የሆነ እንደ ትንሽ ይሁን፤ አለቃ የሆነም እንደ አገልጋይ ይሁን።