ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ! ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ ስለ ሰው ልጅ በነቢያት የተጻፈው ሁሉ በዚያ ይፈጸማል። እርሱ ለአሕዛብ ተላልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም ያፌዙበታል፤ ይሰድቡታል፤ ይተፉበታል። ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፤ ነገር ግን በሦስተኛው ቀን ከሞት ይነሣል።” ደቀ መዛሙርቱ ግን ከዚህ ሁሉ ነገር አንዱንም አልተረዱም፤ የንግግሩም ምሥጢር ተሰውሮባቸው ስለ ነበር ምን ማለቱ እንደ ሆነ አላወቁም። ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ በቀረበ ጊዜ አንድ ዕውር ምጽዋት እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር፤ በአጠገቡ የሚያልፉትን የብዙ ሰዎች ድምፅ በሰማ ጊዜ “ይህ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ። ሰዎቹም “እነሆ! የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ በኩል እያለፈ ነው” ብለው ነገሩት። በዚያን ጊዜ ዐይነ ስውሩ፥ “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ! እባክህ ማረኝ!” እያለ ጮኸ። ቀድመው እፊት እፊት ይሄዱ የነበሩት ሰዎች፦ “ዝም በል!” ብለው ገሠጹት። እርሱ ግን ድምፁን በይበልጥ ከፍ አድርጎ፦ “የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረኝ!” ይል ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ቆመና “ወደ እኔ አምጡት” ብሎ አዘዘ። ዐይነ ስውሩም ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ፥ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” ዐይነ ስውሩም “ጌታ ሆይ! ማየት እፈልጋለሁ” አለው። ኢየሱስም “እይ! እምነትህ አድኖሃል” አለው። ዐይነ ስውሩም ወዲያውኑ ማየት ቻለ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ኢየሱስን መከተል ጀመረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ይህን ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
የሉቃስ ወንጌል 18 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 18:31-43
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos