የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉቃስ ወንጌል 15:25-32

የሉቃስ ወንጌል 15:25-32 አማ05

“በዚህ ጊዜ ታላቁ ልጅ ለሥራ ወደ እርሻ ወጥቶ ነበር፤ ተመልሶ ሲመጣ ወደ ቤቱ በተቃረበ ጊዜ የሙዚቃና የጭፈራ ድምፅ ሰማ፤ ከአገልጋዮቹ አንዱን ጠርቶ ‘ምንድን ነው ነገሩ?’ ብሎ ጠየቀው። አገልጋዩም ‘ወንድምህ ተመልሶ ስለ መጣ ነው፤ አባትህ በደኅና ስላገኘው የሰባውን ወይፈን ዐርዶለታል’ አለው። “ታላቅ ወንድሙም በጣም ተቈጥቶ፥ ‘ወደ ቤት አልገባም’ አለ። ስለዚህ አባቱ ወደ ደጅ ወጥቶ እንዲገባ ለመነው፤ ልጁ ግን ለአባቱ እንዲህ ሲል መለሰ፤ ‘እነሆ! ይህን ያኽል ዓመት አገለገልኩህ፤ ከትእዛዝህም ከቶ ዝንፍ ብዬ አላውቅም፤ ታዲያ እኔ ከጓደኞቼ ጋር የምደሰትበት አንድ ጠቦት እንኳ ሰጥተኸኝ አታውቅም! ይህ ልጅህ ግን ሀብትህን ከአመንዝራ ሴቶች ጋር አባክኖ በተመለሰ ጊዜ የሰባውን ወይፈን ዐረድክለት።’ አባቱም እንዲህ አለው፤ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፤ የእኔ የሆነ ሁሉ የአንተ ነው። ይህ ወንድምህ ግን ሞቶ ነበር፤ አሁን በሕይወት አለ፤ ጠፍቶ ነበር፤ አሁን ተገኘ፤ ስለዚህ በጣም ልንደሰት ይገባናል።’ ”

Free Reading Plans and Devotionals related to የሉቃስ ወንጌል 15:25-32