የሉቃስ ወንጌል 12:1-3

የሉቃስ ወንጌል 12:1-3 አማ05

በዚያን ጊዜ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ ከብዛታቸውም የተነሣ እርስ በርሳቸው እየተጋፉ ይረጋገጡ ነበር፤ ኢየሱስም በቅድሚያ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፤ “ከፈሪሳውያን እርሾ ማለትም ከግብዝነታቸው ተጠንቀቁ ማለት ነው። የተሸፈነ ነገር ሳይገለጥ አይቀርም፤ የተሰወረውም ሳይታወቅ አይቀርም። ስለዚህ በጨለማ የተናገራችሁት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በዝግ ቤት ውስጥ በሹክሹክታ በጆሮ የተናገራችሁትም በሰገነት ላይ በይፋ ይነገራል።