የሉቃስ ወንጌል 10:39-42

የሉቃስ ወንጌል 10:39-42 አማ05

እርስዋ ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፤ ይህች ማርያም በኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጣ ትምህርቱን ታደምጥ ነበር። ማርታ ግን ምግብ በማዘጋጀት በብርቱ ትደክም ነበር፤ ስለዚህ ወደ ኢየሱስ ቀርባ፥ “ጌታ ሆይ! ይህች እኅቴ ሥራውን ሁሉ ለእኔ ትታ ብቻዬን ስደክም እያየህ ዝም ትላለህን? እባክህ እንድታግዘኝ ንገራት!” አለችው። ጌታ ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “ማርታ፥ ማርታ፥ አንቺ በብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትታወኪያለሽም፤ ነገር ግን ተፈላጊው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም የሚሻለውን ነገር መርጣለች፤ እርሱንም ከእርስዋ የሚወስድባት ማንም የለም።”