እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ትሰግዱላቸው ዘንድ ማናቸውንም ዐይነት ጣዖቶች አትሥሩ፤ እንዲሁም ምስል ወይም ሐውልት ወይም የተቀረጸ የድንጋይ ዐምድ አታቁሙ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ ሰንበቶቼን ጠብቁ፤ መቅደሴን አክብሩ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። “በሕጌ ብትመሩና ትእዛዞቼንም ብትጠብቁ፥ ምድራችሁ በሰብል፥ ዛፎቻችሁም በፍሬ የተሞሉ ይሆኑ ዘንድ ዝናብን በወቅቱ እልክላችኋለሁ። ሰብላችሁም እጅግ የበዛ ከመሆኑ የተነሣ ገና መከር መሰብሰብ ሳትጨርሱ፥ የወይን ዘለላ የምትቈርጡበት ጊዜ ይደርሳል፤ የወይን ዘለላም ቈርጣችሁ ሳትጨርሱ እህል የምትዘሩበት ወቅት ይደርሳል፤ ለምግብ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ታገኛላችሁ፤ በምድራችሁም በሰላም ትኖራላችሁ። “በምድራችሁ ሰላምን እሰጣችኋለሁ፤ ማንንም ሳትፈሩ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ አደገኞች የሆኑ አራዊትን ከምድራችሁ አስወግዳለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ጦርነት በዚያ አይኖርም። ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፤ በፊታችሁም በጦርነት ያልቃሉ፤ ከእናንተ አምስቱ መቶውን ጠላት ያሸንፋሉ፤ አንድ መቶው ደግሞ ዐሥሩን ሺህ ድል ይነሣሉ፤ ጠላቶቻችሁም በጦርነት ያልቃሉ። ፊቴን በምሕረት ወደ እናንተ እመልሳለሁ፤ ዘራችሁን አበዛለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ። ገና ያለፈውን ሰብል በመብላት ላይ እያላችሁ፥ ለአዲሱ ሰብል ቦታ ማስለቀቅ ይኖርባችኋል። እኔም መኖሪያዬን በእናንተ መካከል አደርጋለሁ፤ አልጸየፋችሁም። እኔ ከእናንተ ጋር እሄዳለሁ፤ አምላካችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ። በባርነት እንዳትገዙ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ ተጭኖአችሁ የነበረውን የባርነት ቀንበር ሰብሬ፥ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአለሁ።”
ኦሪት ዘሌዋውያን 26 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘሌዋውያን 26:1-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos