የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሰቈቃወ ኤርምያስ 5:1-3

ሰቈቃወ ኤርምያስ 5:1-3 አማ05

እግዚአብሔር ሆይ! በእኛ ላይ የደረሰውን አስብ፤ ውርደታችንንም ተመልከት! ርስታችን ለባዕዳን ተሰጠ፤ ቤታችን ሁሉ የባዕዳን መኖሪያ ሆኖአል፤ አባቶቻችን በጠላት እጅ ተገደሉ፤ ስለዚህ እኛ አባት የሌለን፥ እነሆ እናቶቻችንም ባል አልባ ሆነው ቀርተዋል።