የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሰቈቃወ ኤርምያስ 3:19-33

ሰቈቃወ ኤርምያስ 3:19-33 አማ05

መከራዬንና ከርታታነቴን ማስታወስ እንደ እሬትና እንደ ሐሞት ሆነብኝ። ስለዚህም ሁኔታ ሁልጊዜ ሳስብ መንፈሴ ይጨነቃል፤ ሆኖም ይህን አንድ ነገር በማስብበት ጊዜ በተስፋ እሞላለሁ። ይኸውም ሳንጠፋ የቀረነው የእግዚአብሔር ምሕረት ከቶ የማያቋርጥና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ ነው። እነርሱ በየማለዳው ይታደሳሉ፤ ስለዚህ የአንተ ታማኝነት ታላቅ ነው። የእኔ አለኝታ እግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ እርሱን ብቻ ተስፋ አደርጋለሁ። እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠባበቁትና እርሱን ለሚፈልጉ መልካም ነው። ሰው የእግዚአብሔርን አዳኝነት ጸጥ ብሎ መጠበቁ መልካም ነው። ሰው በወጣትነቱ መከራን በትዕግሥት ቢቀበል መልካም ነው። እግዚአብሔር መከራውን በሚአመጣበት ጊዜ ጸጥ ብሎ ለብቻው ቢቀመጥ መልካም ነው። እንደገና ተስፋ ሊኖር ስለሚችል ራሱን ዝቅ አድርጎ ያስገዛ። ለሚመታው ጒንጩን ይስጥ፤ ስድብንም ይቀበል። ይህን ሁሉ ቢያደርግ እግዚአብሔር ለዘለዓለም አይተወውም። ምንም እንኳ ጭንቀት በሰው ላይ እንዲደርስ ቢፈቅድ ከተትረፈረፈ ዘለዓለማዊ ፍቅሩ የተነሣ ይራራል። ይህም የሚሆነው እርሱ በራሱ ፍላጎት በሰው ላይ ችግርንና ሐዘንን ስለማያመጣ ነው።