እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ! የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ከዚህ በፊት የተናገሩትን ቃል አስታውሱ። እነርሱ “በመጨረሻው ዘመን ከእግዚአብሔር ፈቃድ የራቁ የገዛ ራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ ፌዘኞች ይመጣሉ” ብለዋችሁ ነበር። እነርሱ ሰውን የሚለያዩ፥ የሥጋን ምኞት የሚከተሉ፥ መንፈስ ቅዱስ የሌላቸው ሰዎች ናቸው። እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ በላይ በተቀደሰው እምነታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ ትጉ፤ በመንፈስ ቅዱስም ኀይል ጸልዩ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በምሕረቱ ወደ ዘለዓለም ሕይወት እንዲያደርሳችሁ በመጠባበቅ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ጠብቁት።
የይሁዳ መልእክት 1 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የይሁዳ መልእክት 1:17-21
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos