መጽሐፈ ኢያሱ 4:19-24

መጽሐፈ ኢያሱ 4:19-24 አማ05

ሕዝቡ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን፥ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ በኩል በሚገኘው በጌልገላ ሰፈሩ። በጌልገላም ኢያሱ ከዮርዳኖስ ወንዝ የተወሰዱትን ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አቁሞ፥ ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ አለ፦ “በሚመጡት ዘመናት የልጅ ልጆቻችሁ፦ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብለው ወላጆቻቸውን በሚጠይቁአቸው ጊዜ፦ የእስራኤል ሕዝብ የዮርዳኖስን ወንዝ በደረቅ ምድር የተሻገሩበት ጊዜ መኖሩን ትነግሩአቸዋላችሁ፤ አምላካችን እግዚአብሔር እስክንሻገር ድረስ አስቀድሞ ለእኛ የቀይ ባሕርን እንዳደረቀልን፥ ለእናንተም የዮርዳኖስን ወንዝ እስክትሻገሩ ድረስ ውሃ አድርቆ ያሻገራችሁ መሆኑን ንገሩአቸው፤ በዚህም ምክንያት በምድር ላይ የሚኖር ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔር ኀይል ምን ያኽል ታላቅ እንደ ሆነ ይገነዘባል፤ እናንተም አምላካችሁ እግዚአብሔርን ለዘለዓለም ታከብራላችሁ።”