ትንቢተ ዮናስ 2:1-6

ትንቢተ ዮናስ 2:1-6 አማ05

ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ እንዲህ ሲል ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ “እግዚአብሔር ሆይ! ተጨንቄ ሳለሁ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ አንተም መለስክልኝ፤ ርዳታህን ለማግኘት ጥልቅ ከሆነው ከሙታን ዓለም ወደ አንተ ጮኽኩ፤ አንተም ሰማኸኝ። ጥልቅ ወደ ሆነው ወደ ባሕር መሠረት ጣልከኝ፤ በዙሪያዬም ውሃ ከበበኝ፤ ማዕበልህና ሞገድህ በላዬ ላይ አለፉ። እኔ ከፊትህ የጠፋሁ ነኝ፤ ይሁን እንጂ ቅዱስ መቅደስህን እንደገና አያለሁ። ውሃ እስከ አንገቴ ድረስ አጠለቀኝ፤ ባሕርም ፈጽሞ አሰጠመኝ፤ በባሕር ውስጥም የበቀለው ሣር ቅጠል በራሴ ላይ ተጠመጠመብኝ። ወደ ተራራዎች ሥር ወረድኩ፤ ከዚያ በታች ባለው ምድርም ውስጥ ለዘለዓለም ሊዘጋብኝ ነበር፤ አንተ ግን እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እኔን ከጥልቁ ውሃ አውጥተህ ሕይወቴን ታድናለህ።