ትንቢተ ኢዩኤል መግቢያ
መግቢያ
ነኢቢዩ ኢዩኤል መቼ እንደ ኖረና በአጠቃላይም ስለ ሕይወት ታሪኩ ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም፤ ይሁን እንጂ መጽሐፉ የተገኘው ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ወይም በአራተኛው ምእት ዓመት አካባቢ እንደ ሆነ ይገመታል፤ ይህም ጊዜ በፋርስ ዘመነ መንግሥት መሆኑ ነው። ኢዩኤል በእስራኤል ምድር ታላቅ የአንበጣ መንጋ የሚመጣበትንና ብርቱ ጥፋት የሚያስከትል ድርቅ የሚከሠትበትን ጊዜ ይገልጣል፤ እነዚህ ሁኔታዎችም የጌታን ቀን መምጣት መቃረብ የሚያመለክቱ መሆኑን ይናገራል፤ የጌታም ቀን ሲመጣ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱን የሚቃወሙትን ሁሉ እንደሚቀጣ ጨምሮ ያስረዳል። ነቢዩ፥ ሕዝቡ ንስሓ እንዲገባ የእግዚአብሔርን ጥሪ በመግለጽ፥ ንስሐ ከገቡም ወደ ቀድሞው ሁኔታቸው በመመለስ እንደሚባርካቸው ያስገነዝባቸዋል። ከትንቢቱ ውስጥ ጐልቶ የሚታየው የተስፋ ቃል እግዚአብሔር በወንዶችና በሴቶች፥ በወጣቶችና በሽማግሌዎች ጭምር በሕዝቡ ሁሉ ላይ መንፈሱን እንደሚያወርድ የሚገልጠው ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. አንበጣና የጠላት ጦር ሠራዊት (1፥1—2፥17)
2. የጌታ ቀን (2፥18-32)
3. ጌታ አሕዛብን እንደሚቀጣ (3፥1-21)
Currently Selected:
ትንቢተ ኢዩኤል መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997