የቴማን አገር ሰው የሆነው ኤሊፋዝ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ኢዮብ ሆይ! አንድ ሰው ደፍሮ ቢናገርህ በትዕግሥት ታዳምጣለህን? ነገር ግን ከመናገር ማን ይቈጠባል? ብዙ ሰዎችን አስተምረሃል፤ የደከሙትንም እጆች አበርትተሃል። ቃሎችህ የሚሰናከሉትን ይደግፉ ነበር፤ የሚብረከረኩትንም ጒልበቶች ታበረታ ነበር። አሁን ግን ችግር ስለ መጣብህ ተስፋ ቢስ ሆነሃል፤ ችግሩም ስለ በረታብህ ተስፋ ቈርጠሃል። አምላክህን መፍራትህ መተማመኛህ፥ ትክክለኛ መንገዶችህም፥ ተስፋህ አይደለምን? ንጹሕ ሰው ሆኖ መከራ የደረሰበት፥ ቀጥተኛ ሰው ሆኖ ሳለ የተደመሰሰ እንዳለ እስቲ አስብ። እኔ እንዳስተዋልኩት ክፋትን የሚያርሱና መከራን የሚዘሩ ያንኑ ይሰበስባሉ።
መጽሐፈ ኢዮብ 4 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ኢዮብ 4:1-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች