ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮብን እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር “ይህ፥ ያለ ዕውቀት በሚነገሩ ቃላት ምክሬን የሚያቃልል እርሱ ማነው? እስቲ በፊቴ እንደ ወንድ ታጠቅ፤ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም መልስልኝ። ለመሆኑ ዓለምን ስፈጥር አንተ በዚያ ነበርክን? የምታውቅና የምታስተውል ከሆነ እስቲ ንገረኝ። የምድርን መጠን የወሰነ ማን ነው? በእርሱዋ ላይስ የመለኪያ መስመሮችን የዘረጋ ማን እንደ ሆነ ታውቃለህን? የምድርን ምሰሶዎች አጽንቶ የያዘ ኀይል ምንድን ነው? የዓለምንስ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠ ማን ነው? የንጋት ከዋክብት በአንድነት ሲዘምሩ፥ መላእክትም ሁሉ እልል ሲሉ አንተ የት ነበርክ? “ከምድር ውስጥ ፈንድቶ በወጣ ጊዜ የመፍለቂያ በሮቹን የዘጋ ማነው? ባሕርን በደመና የጋረድኩ በድቅድቅ ጨለማም የሸፈንኩ እኔ ነኝ። ለባሕር ወሰንን የሠራሁ፥ በርና ገደብም እንዲኖረው ያደረግኹ እኔ ነኝ።
መጽሐፈ ኢዮብ 38 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ኢዮብ 38:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos