መጽሐፈ ኢዮብ 28:20-28

መጽሐፈ ኢዮብ 28:20-28 አማ05

ታዲያ፥ ጥበብ ከየት ትመጣለች? ማስተዋልስ ከወዴት ትገኛለች? “ከሕያው ፍጡር ሁሉ የተሰወረች ናት፤ በሰማይ የሚበሩ ወፎች እንኳ ፈልገው አያገኙአትም። ጥፋትና ሞት ‘ስለ እርስዋ የምናውቀው፥ በወሬ ብቻ ነው’ ይላሉ። “ወደ ጥበብ የሚወስደውን መንገድና መኖሪያ ቦታዋንም የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ነው። እርሱም የምድርን ዳርቻ ሁሉ ይመለከታል፤ ከሰማይ በታች ያለውን ሁሉ ያያል። የነፋስን ኀይል በመሠረተ ጊዜ፥ የውቅያኖስን ውሃ በሰፈረ ጊዜ፥ ዝናብና ለነጐድጓዳዊ መብረቅ ሥርዓትን በደነገገ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ጥበብን ተመለከታት ገምግሞም አከበራት፤ መርምሮም አጸናት። “በዚያን ጊዜ ሰውን ‘እነሆ፥ ጥበብ ማለት እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ማስተዋልም ማለት ከክፋት መራቅ ነው’ ብሎታል።”

YouVersion የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን ይጠቀማል። የእኛን ድረ ገጽ በመጠቀም፣ በግለሰብነት መመሪያችን ላይ እንደተገለጸው የእኛን የኩኪዎች አጠቃቀም ተቀብለዋል