የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 17

17
1“መንፈሴ ደከመ፤
የሕይወቴም ዘመን ሊፈጸም ተቃርቦአል፤
መቃብርም ይጠብቀኛል።
2የሚሳለቁብኝ ከበቡኝ
ዐይኔም የእነርሱን ጥላቻ ይመለከታል።
3አምላክ ሆይ! ከአንተ በቀር ለእኔ የሚቆምልኝ የለምና
አንተው ራስህ ተያዥ ሁነኝ።
4እነርሱ ተመራምረው ማስተዋል እንዳይችሉ፥
አእምሮአቸውን ዘግተሃል፤
ስለዚህ ድልን እንዲቀዳጁ አታድርግ።
5ገንዘብ ለማግኘት ብሎ
ባልንጀራውን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥
ግፉ በልጆቹ ላይ ይደርሳል።
6እግዚአብሔር የሰዎች መዘባበቻ አደረገኝ፤
ሰዎቹም በፊቱ እንደሚተፉበት ሰው ሆንኩ።
7ከሐዘን የተነሣ ዐይኖቼ ፈዘዋል፤
መላ ሰውነቴም እንደ ጥላ ሆኖአል።
8እውነተኞች በዚህ ነገር ተደናግጠዋል፤
ንጹሖች እግዚአብሔርን በማያምኑ ሰዎች ላይ ተቈጥተዋል።
9ይሁን እንጂ ጻድቃን ከእውነት መንገድ ፈቀቅ አይሉም፤
ንጹሖችም በብርታት ላይ ብርታትን ይጨምራሉ።
10ሁላችሁም እንደገና መጥታችሁ በፊቴ ብትከራከሩ
ከመካከላችሁ አንድ እንኳ አስተዋይ ሰው አላገኝም።
11“የዕድሜዬ ዘመን ተፈጽሞአል፤
ዕቅዴና የልቤ ምኞት ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል።
12እነዚህ ሰዎች ሌሊቱን ቀን ነው ይላሉ፤
ብርሃኑን ደግሞ ሊጨልም ነው ይላሉ።
13ከእንግዲህ ወዲህ የሚኖረኝ ዕድል ፈንታ
ወደ ሙታን ዓለም መውረድ ነው፤
እዚያም በጨለማ አልጋዬን እዘረጋለሁ።
14መቃብርን ‘አባቴ’ ብዬ እጠራዋለሁ፤
የሚበሉኝንም ትሎች ‘እናቴና እኅቴ’ እላቸዋለሁ።
15ታዲያ፥ እኔ ምን ተስፋ አለኝ?
ተስፋ የሚሆነኝንስ ነገር ማን ያይልኛል?
16እኔ ወደ ሲኦል ስወርድ ተስፋ አብሮኝ ይወርዳልን?
አብረንስ ወደ መቃብር እንወርዳለንን?”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ