የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 11

11
ጾፋር
1ናዕማታዊውም ጾፋር እንዲህ አለ፦
2“ለዚህ ሁሉ ከንቱ ቃል መልስ የሚሰጥ የለምን?
አንድ ሰው ይህን ያኽል በመለፍለፍ ትክክለኛ ሊሆን ይችላልን?
3ኢዮብ ሆይ! ከንቱ ንግግርህ መልስ የማይሰጥበት ይመስልሃልን?
ይህን ያኽልስ ስታፌዝ፥ የሚገሥጽህ የሌለ መሰለህን?
4በሐሳብህ ‘ትክክለኛ ነኝ’ ትላለህ፤
ለእግዚአብሔርም ‘በፊትህ
ንጹሕ ነኝ’ ትለዋለህ።
5ምነው እግዚአብሔር በተናገረና
ትክክለኛውን መልስ በሰጠህ!
6የጥበብ መንገድ ብዙ ስለ ሆነ፥
ምነው ጌታ የጥበብን ምሥጢር ቢገልጥልህ!
ስለዚህ እግዚአብሔር የቀጣህ፥
ከሚገባህ አሳንሶ መሆኑን ዕወቅ።
7“የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምሥጢር ማወቅ ትችላለህን?
ሁሉን ቻይ አምላክንስ መርምረህ ልትደርስበት ትችላለህን?
8የእርሱ ታላቅነት ከሰማይ በላይ ነው፤
አንተ ምን ልታደርግ ትችላለህ?
ጥልቀቱም ከሲኦልም በታች ነው፤ አንተ ምን ታውቃለህ?
9የእግዚአብሔር ታላቅነት ከምድር ይረዝማል፤
ከባሕርም ይሰፋል።
10እግዚአብሔር መጥቶ ቢያስር፥
ወደ ፍርድ ሸንጎም ቢያቀርብ፥
ማን ይከለክለዋል?
11እግዚአብሔር የማይጠቅሙ ሰዎችን ያውቃቸዋል፤
በደልን በሚያይበት ጊዜ ዝም ብሎ አይመለከትም።
12ሞኝ ሰው ጥበበኛ ከሚሆን ይልቅ
የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ቢወለድ ይቀላል።
13“ሆኖም፥ ልብህን የቀና ብታደርግ
እጅህንም ዘርግተህ ወደ እግዚአብሔር ብትጸልይ፥
14ኃጢአትን ከእጅህ ብታርቅ፥
ክፉ ነገርም በቤትህ እንዲገኝ ባታደርግ፥
15በዚያን ጊዜ ቀና ብለህ
ያለ ኀፍረት ሁሉን ነገር ታያለህ፤
ያለ ፍርሀትም ጸንተህ መቆም ትችላለህ።
16ችግርህን ሁሉ ትረሳዋለህ፤
የምታስታውሰውም እንዳለፈ
ጐርፍ ብቻ ነው።
17ሕይወትህ ከቀትር ፀሐይ ይበልጥ ይበራል፤
ጨለማው እንደ ማለዳ ብርሃን ይሆናል።
18ተስፋ ስላለህ አንተም በመተማመን ትኖራለህ፤
እግዚአብሔር ስለሚጠብቅህ ያለ ስጋት ዐርፈህ ትኖራለህ።
19ማንንም ሳትፈራ ትተኛለህ፤
ብዙ ሰዎችም በአንተ ፊት ሞገስ ማግኘትን ይፈልጋሉ።
20የክፉዎች ዐይን ይታወራል፤
የማምለጫ መንገዳቸው ሁሉ የተዘጋ ነው፤
የእነርሱም መጨረሻ ሞት ነው።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ