እኔ ከአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተ ግን ከአባታችሁ የሰማችሁትን ታደርጋላችሁ።” እነርሱም “አባታችን አብርሃም ነው” ሲሉ መለሱለት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የአብርሃም ልጆችስ ብትሆኑ ኖሮ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም። እንግዲህ እናንተ የምትሠሩት የአባታችሁን ሥራ ነው።” እነርሱም “እኛ በምንዝር የተወለድን ዲቃላዎች አይደለንም፤ አንድ አባት አለን፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆንማ እኔን በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ወደዚህ የመጣሁት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ የላከኝ እርሱ ነው እንጂ እኔ በራሴ ሥልጣን አልመጣሁም። ስለ ምን ንግግሬ አይገባችሁም? ንግግሬን ለመስማት ስለማትችሉ ነው። እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች ናችሁ፤ ፍላጎታችሁም የአባታችሁን ምኞት መፈጸም ነው፤ እርሱ ከመጀመሪያ አንሥቶ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነት በእርሱ ስለሌለ ከእውነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ እርሱ ሐሰተኛና የሐሰት ሁሉ አባት ስለ ሆነ ሐሰት በሚናገርበት ጊዜ ከገዛ ራሱ አውጥቶ ይናገራል። እኔ ግን እውነትን ስለምናገር አታምኑኝም፤ ለመሆኑ ከእናንተ ‘ኃጢአተኛ ነህ’ ብሎ የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነትን የምናገር ከሆንኩ ታዲያ፥ ለምን አታምኑኝም? ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፤ እንግዲህ እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል የማትሰሙት ከእግዚአብሔር ስላልሆናችሁ ነው።” አይሁድ “አንተ ሳምራዊ ነህ፤ ጋኔንም አለብህ፤ ማለታችን ልክ አይደለምን?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ ጋኔን የለብኝም፤ ነገር ግን አባቴን አከብራለሁ፤ እናንተ ግን ታዋርዱኛላችሁ። ይሁን እንጂ እኔ የራሴን ክብር አልፈልግም፤ የእኔን መከበር የሚፈልግና የሚፈርድ ሌላ አለ። እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ፈጽሞ አይሞትም።” አይሁድ እንዲህ አሉት፦ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን ዐወቅን፤ አብርሃም እንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ አይሞትም’ ትላለህ፤ ለመሆኑ አንተ ከሞተው ከአባታችን ከአብርሃም ትበልጣለህን? ነቢያት ሞተዋል፤ ታዲያ፥ አንተ ራስህን ማንን ታደርጋለህ?” ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ራሴን ባከብር ክብሬ ዋጋ አይኖረውም እኔን የሚያከብረኝ አባቴ ነው፤ እርሱም ‘እናንተ አምላካችን’ የምትሉት ነው። ሆኖም እናንተ እርሱን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ እኔ አላውቀውም ብል እንደ እናንተ ሐሰተኛ በሆንኩ ነበር፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ። የአባታችሁ የአብርሃም ምኞት የእኔን ቀን አይቶ ለመደሰት ነበር፤ አይቶም ተደሰተ።” በዚህ ጊዜ አይሁድ፥ “አንተ ገና ኀምሳ ዓመት እንኳ አልሆነህም፤ ታዲያ እንዴት አብርሃምን አየሁ ትላለህ?” አሉት። ኢየሱስም “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ ነበርኩ፤ አሁንም፥ ወደፊትም አለሁ።” አላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 8 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ወንጌል 8:38-58
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos