ኢየሱስም “ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ተመለሺ” አላት። ሴትዮዋም “ባል የለኝም” ስትል መለሰች፤ በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላት፦ “ባል የለኝም ማለትሽ ልክ ነው፤ አምስት ባሎች ነበሩሽ፤ አሁንም ከአንቺ ጋር ያለው ሰው ባልሽ አይደለም፤ ስለዚህ እውነቱን ተናግረሻል።” ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ “ጌታ ሆይ! አንተ ነቢይ እንደ ሆንክ አሁን ዐወቅሁ፤ አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ ሰገዱ፤ እናንተ ግን ‘ሰዎች ሊሰግዱ የሚገባቸው በኢየሩሳሌም ነው’ ትላላችሁ።” ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “አንቺ ሴት፥ በዚህ ተራራ ላይ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ እንደሚመጣ እመኚኝ፤ እናንተ ለማታውቁት አምላክ ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ግን መዳን የሚመጣው ከአይሁድ ስለ ሆነ ለምናውቀው አምላክ እንሰግዳለን። ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ፥ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል፤ እንዲያውም አሁን መጥቶአል፤ አብም የሚፈልገው በዚህ መንገድ የሚሰግዱለትን ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባቸዋል።” ሴትዮዋም “ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንደሚመጣ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ነገር ይነግረናል” አለችው። ኢየሱስም “እነሆ! አሁን የማነጋግርሽ እኔ እርሱ ነኝ” አላት።
የዮሐንስ ወንጌል 4 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ወንጌል 4:16-26
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos