የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮሐንስ ወንጌል 19:14-16

የዮሐንስ ወንጌል 19:14-16 አማ05

የፋሲካ በዓል የዝግጅት ቀን ነበረ፤ ጊዜውም ወደ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ፤ በዚያን ጊዜ ጲላጦስ አይሁድን “እነሆ ንጉሣችሁ!” አላቸው። እነርሱ ግን “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “ንጉሣችሁን ልስቀለውን?” አላቸው። የካህናት አለቆችም “ከሮማው ንጉሠ ነገሥት በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም!” ሲሉ መለሱለት። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲሰቀል ጲላጦስ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ኢየሱስን ይዘው ወሰዱት።