የዮሐንስ ወንጌል 15:14-16

የዮሐንስ ወንጌል 15:14-16 አማ05

እናንተም እኔ የማዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ። አገልጋይ ጌታው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ከእንግዲህ ወዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጥኩላችሁ ወዳጆቼ ብያችኋለሁ፤ እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።