በማግስቱ ለፋሲካ በዓል የመጡ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም የሚመጣ መሆኑን ሰሙ። ስለዚህ የዘንባባ ቅርንጫፍ ይዘው ሊቀበሉት ወጡ፤ “ሆሳዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው!” እያሉ ይጮኹ ነበር። ኢየሱስ የአህያ ውርንጭላ አገኘና በእርሱ ላይ ተቀመጠ፤ ይህም የሆነው፥ “አንቺ የጽዮን ከተማ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ አትፍሪ! እነሆ! ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ተብሎ የተጻፈው ትንቢት እንዲፈጸም ነው። ደቀ መዛሙርቱ ይህ ነገር በመጀመሪያ አልገባቸውም ነበር፤ ግን ኢየሱስ በክብር ወደ ሰማይ ባረገ ጊዜ ይህ ነገር ስለ እርሱ እንደ ተጻፈና ለእርሱም እንደ ተደረገለት አስታወሱ።
የዮሐንስ ወንጌል 12 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ወንጌል 12:12-16
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos