ትንቢተ ኤርምያስ 47
47
ስለ ፍልስጥኤም የተነገረ ትንቢት
1የግብጽ ንጉሥ በጋዛ ላይ አደጋ ከመጣሉ በፊት እግዚአብሔር ስለ ፍልስጥኤም እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦ #ኢሳ. 14፥29-31፤ ሕዝ. 25፥15-17፤ ኢዩ. 3፥4-8፤ አሞጽ 1፥6-8፤ ሶፎ. 2፥4-7፤ ዘካ. 9፥5-7።
2እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
“እነሆ፥ ውሃ ከሰሜን በኩል ተነሥቶ
በጐርፍ እንደ ተሞላ ወንዝ ይፈስሳል፤
ምድርንና በምድር ላይ ያለውን ሁሉ
ከተሞችንና በውስጣቸው የሚኖሩትን ሕዝብ በሙሉ ይሸፍናል።
ሕዝቡ ሁሉ ርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤
በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ምርር ብለው ያለቅሳሉ።
3ከሚጋልቡ ፈረሶች ኮቴ ድምፅ፥
ከጠላት መንኰራኲር ድምፅ፥
ከሠረገሎቻቸው መትመም የተነሣ
አባቶች ኀይላቸው በመድከሙ ምክንያት
ልጆቻቸውን እንኳ ለመርዳት ወደ ኋላ አይመለሱም።
4ፍልስጥኤም የምትጠፋበት ጊዜ ደርሶአል፤
ከሞት ተርፈው ጢሮስንና ሲዶናን የሚረዱት ሁሉ
ተቈራርጠው የሚቀሩበት ጊዜ ተቃርቦአል።
እኔ እግዚአብሔር፥ ከሞት ተርፈው በባሕር ዳርቻ የምትገኘው
የካፍቶር ዘሮች የሆኑትን ፍልስጥኤማውያን በሙሉ እደመስሳለሁ።
5የጋዛ ሕዝብ በሐዘን ጠጒራቸውን ይላጫሉ፤
የአስቀሎና ሕዝብ ሁሉ ጸጥ እንዲሉ ይደረጋሉ።
በፍልስጥኤም ሸለቆ ከጥፋት የተረፉትስ
ሰውነታቸውን እየቈራረጡ የሚያዝኑት እስከ መቼ ነው?
6‘የእግዚአብሔር ሰይፍ ሆይ! ከሥራህ የምታርፈው መቼ ነው?
እባክህ ወደ አፎትህ ተመልሰህ ዕረፍት አድርግ’ እያላችሁ ትጮኻላችሁ።
7ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር የሰጠሁትን ሥራ ሳይፈጽም እንዴት ማረፍ ይችላል?
እኔ በአስቀሎናና በጠረፎችዋ በሚኖሩ ሕዝብ ላይ አደጋ እንዲጥል አዝዤዋለሁ።”
Currently Selected:
ትንቢተ ኤርምያስ 47: አማ05
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997