የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ኤርምያስ 12:1-4

ትንቢተ ኤርምያስ 12:1-4 አማ05

እግዚአብሔር ሆይ! ከአንተ ጋር በምከራከርበት ጊዜ ሁሉ አንተ ትክክለኛ ነህ፤ አሁን ግን ስለ ትክክለኛ ፍርድ ጥያቄ አለኝ፤ የኃጢአተኛ ሕይወት የተቃና የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? አታላዮችስ ሁሉ ነገር የሚሳካላቸው ስለምንድን ነው? አንተ ተክለሃቸዋል፤ እነርሱም ሥር ሰደዋል፤ አድገውም ፍሬ ያፈራሉ፤ በአፋቸው ያከብሩሃል፤ ልባቸው ግን ከአንተ የራቀ ነው። እግዚአብሔር ሆይ! እኔን ግን ታውቀኛለህ፤ ስለ አንተ ያለኝን አስተሳሰብ አይተህ ትፈትነኛለህ፤ እነዚህን ክፉ ሰዎች እንደሚታረዱ በጎች ውሰዳቸው፤ ለዕርድም ቀን ለይተህ አቈያቸው። “እኛ የምናደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር አያይም” ከሚሉት ሕዝባችን ክፋት የተነሣ፥ ምድራችንን ድርቅ የሚያጠቃውና በየመስኩ ያለውስ ሣር እንደ ደረቀ የሚቀረው እስከ መቼ ነው? በዚህም ምክንያት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ተጠራርገው ጠፍተዋል።