ወንድሞቼ ሆይ! እኛ አስተማሪዎች የሆንን የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል ታውቃላችሁና ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ። እኛ ሁላችን ብዙ ጊዜ እንሳሳታለን፤ በንግግሩ የማይሳሳት እርሱ ሰውነቱን መቈጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው። ፈረስ እንዲታዘዝልን በአፉ ውስጥ ልጓም እናገባለን፤ ፈረሱንም ወደምንፈልገው ቦታ እንመራዋለን። መርከብ ምንም ትልቅ ቢሆንና በኀይለኛ ነፋስ የሚገፋ ቢሆንም፥ የመርከቡ ነጂ በትንሽ መቅዘፊያ ወደ ፈለገው ቦታ ይነዳዋል። እንዲሁም ምላስ ትንሽ የአካል ክፍል ስትሆን በታላላቅ ነገሮች ትመካለች፤ ትልቅ ጫካ የሚቃጠለው በትንሽ እሳት ነው። ምላስም እንደ እሳት ናት፤ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ ክፉ ዓለም ናት፤ አካላችንን ትበክላለች፤ ከገሃነም እንደሚወጣ እሳትም የኑሮአችንን ሂደት ሁሉ ታቃጥላለች።
የያዕቆብ መልእክት 3 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የያዕቆብ መልእክት 3:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos