ወንድሞቼ ሆይ! ሰው እምነት አለኝ ቢል፥ ነገር ግን እምነቱን በመልካም ሥራ ባይገልጥ ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ለምሳሌ የሚለብሱትና የሚመገቡት የሌላቸው ወንድሞችና እኅቶች ቢኖሩ፥ ከእናንተ አንዱ ለኑሮአቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሳይሰጣቸው “በሰላም ሂዱ! ይሙቃችሁ! ጥገቡ!” ቢላቸው ምን ይጠቅማቸዋል? ከመልካም ሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው። ነገር ግን “አንተ እምነት አለህ፤ እኔም መልካም ሥራ አለኝ” የሚል ቢኖር፥ “እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም በሥራዬ እምነቴን አሳይሃለሁ” እለዋለሁ። አንተ “አንድ እግዚአብሔር አለ” ብለህ ታምናለህ፤ ይህም መልካም ነው፤ ማመንማ አጋንንትም ያምናሉ፤ በፍርሃትም ይንቀጠቀጣሉ። አንተ ሞኝ! እምነት ያለ ሥራ ፍሬቢስ መሆኑን ታያለህን? አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበው ጊዜ የጸደቀው በሥራ አይደለምን? ስለዚህ እምነት ከሥራው ጋር አብሮ እንደ ነበርና እምነትም በሥራ ፍጹም እንደ ሆነ ታያለህን? በቅዱስ መጽሐፍ “አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፤ እምነቱም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” የተባለው ቃል ተፈጸመ፤ በዚህ ሁኔታ አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ ተባለ። እንግዲህ ሰው የሚጸድቀው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም ጭምር መሆኑን ታያለህ። አመንዝራይቱ ረዓብ የእስራኤልን መልእክተኞች በቤትዋ በተቀበለች ጊዜና በሌላም መንገድ እንዲሄዱ ባደረገቻቸው ጊዜ እርስዋስ በሥራዋ ጸድቃ የለምን? አካል ያለ ነፍስ የሞተ ነው፤ እንዲሁም ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።
የያዕቆብ መልእክት 2 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የያዕቆብ መልእክት 2:14-26
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos