እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመረጥኳችሁ አገልጋዮቼ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! አድምጡ። በማሕፀን የሠራኋችሁና የምረዳችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ አገልጋዮቼ ስለ ሆናችሁና እኔ ስለ መረጥኳችሁ አትፍሩ። “ለተጠማው ምድር ውሃን እሰጣለሁ፤ በደረቀውም ምድር ጅረቶች እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፤ መንፈሴን በልጆችህ ላይ አፈሳለሁ፤ በረከትንም ለልጅ ልጆችህ እሰጣለሁ። እነርሱ ውሃ በደንብ እንደ ጠጣ ሣር፥ በወራጅ ምንጮች አጠገብ እንዳለ የአኻያ ዛፍ ሁልጊዜ የለመለሙ ይሆናሉ። “አንዱ ‘እኔ የእግዚአብሔር ነኝ’ ይላል፤ ሌላው በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ሌላው ደግሞ ‘የእግዚአብሔር ሰው ነኝ’ ብሎ በእጁ ላይ ይነቅሳል፤ እስራኤል በሚለውም ስም ይጠራል።” የሠራዊት አምላክ፥ የእስራኤል ንጉሥና አዳኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እኔ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም። እንደ እኔ ያለ ማነው? እስቲ ካለ ይናገር፤ እስቲ ማስረጃውን በፊቴ ያቅርብ፤ ወደፊት የሚሆነውን አስቀድሞ የተናገረ ማነው? እስቲ ወደፊት የሚሆነውን ይናገር። እናንተ አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ ከጥንት ዘመናት ጀምሮ አስቀድሜ አልነገርኳችሁምን? ወይስ አልገለጽኩላችሁምን? ለዚህም እናንተ ምስክሮቼ ናቸሁ፤ ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ከእኔ ሌላ መጠጊያ አለት የለም፤ ማንም የለም።”
ትንቢተ ኢሳይያስ 44 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ኢሳይያስ 44:1-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos