ትንቢተ ኢሳይያስ 42:5-9

ትንቢተ ኢሳይያስ 42:5-9 አማ05

ሰማይን የፈጠረና ከዳር እስከ ዳር የዘረጋው፥ ምድርንና በውስጥዋ የሚኖሩትን ሁሉ የሠራ፥ ሕይወትንና እስትንፋስንም የሰጣቸው፥ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤ እጅህን ይዤ ጠብቄሃለሁ፤ ለወገኖቼ እንደ ቃል ኪዳን፥ ለአሕዛብ እንደ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ። ስለዚህ የዕውሮችን ዐይን ታበራለህ፤ በጨለማው ጒድጓድ እስር ቤት ውስጥ ያሉትን እስረኞችን ታወጣለህ። “ስሜ እግዚአብሔር ነው፤ የእኔንም ክብር የሚጋራ ሌላ አምላክ የለም፤ ጣዖቶችም ምስጋናዬን እንዲካፈሉ አልፈቅድም። እነሆ፥ እኔ አስቀድሜ የተናገርኳቸው ነገሮች ሁሉ ተፈጽመዋል፤ አሁን ደግሞ ወደ ፊት ስለሚሆኑት አዳዲስ ነገሮች፥ ከመፈጸማቸው በፊት እናገራለሁ።”