የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ኢሳይያስ 15

15
በሞአብ ላይ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል
1ስለ ሞአብም የተነገረው ቃል ይህ ነው፤ #ኢሳ. 25፥10-12፤ ኤር. 48፥1-47፤ ሕዝ. 25፥8-11፤ አሞጽ 2፥1-3፤ ሶፎ. 2፥8-11።
የዔርና ቂር ከተሞች በአንድ ቀን ሌሊት ተደመሰሱ፥ የሞአብ ምድር ጭር አለች፤ 2የጺቦን ሕዝብም በቤተ ጣዖታቸው ለማልቀስ ወደ ኰረብታ ይወጣሉ፤ የሞአብ ሕዝብ ስለ ነቦና ስለ ሜዳባ ከተሞቻቸው በከባድ ሐዘን ያለቅሳሉ፤ ከሐዘናቸውም የተነሣ ጠጒራቸውንና ጢማቸውን ተላጭተዋል። 3በየመንገዱ የሚታዩት ማቅ ለብሰው ነው፤ በሰገነቶቻቸውና በአደባባዮቻቸው ሁሉም እንባቸውን እያፈሰሱ ያለቅሳሉ። 4የሐሴቦንና የኤልዓሌ ሕዝቦች ይጮኻሉ፤ የጩኸታቸውም ድምፅ እስከ ያሐጽ ድረስ ይሰማል፥ የሞአብ ወታደሮች ሳይቀሩ ወኔያቸው ከድቶአቸው በፍርሃት ተርበደበዱ። 5ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ። 6የኒምሪም ወንዞች ደርቀዋል፤ ምንም ልምላሜ ሳይቀር በአጠገቡ ያለው ሣር ደርቆአል። 7ሕዝቡ የሰበሰቡትን ሀብት እንደ ያዙ የአኻያ ዛፍ የበቀለበትን ሸለቆ ተሻግረው ይሄዳሉ፤ 8በሞአብ ጠረፎች በየስፍራው ጩኸት ይሰማል፤ ጩኸቱም እስከ ኤግላይምና እስከ ብኤርኤሊም ደርሶአል። 9በዲቦን ከተማ የሚገኘው ወንዝ በደም የተሞላ ነው፤ ሆኖም በዲቦን ላይ እግዚአብሔር ከዚያ የባሰ ነገር ያመጣል፤ ከሞአብ ሸሽተው የሚያመልጡትንና እዚያም ከሞት የተረፉትን ሁሉ አንበሳ ልኮ ያጠፋቸዋል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ